ኢትዮጵያውያን በቶክዮን ማራቶን በሁለቱም ጾታ ድርብ ድል ተጎናጽፈዋል።
ዛሬ በተካሄደው የ2019 የቶኪዮ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን በሴቶች ከአንድ እስከ ሶስት እንዲሁም በወንዶች አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች ብርሃኑ ለገሰ: በሴቶች ደግሞ ሩቲ አጋ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል፡፡
በተጨማሪም አትሌት ሄለን ቶላና ሹሬ ደምሴ በሴቶች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች
1ኛ ብርሀኑ ለገሰ ኢቲዮጵያዊ 02:04:48
2ኛ በዳን ካሮኪ ኬንያዊ 02:06:48
3ኛ ዲክሰን ቾምባ ኬንያዊ 02:08:44
በሴቶች
1ኛ ሩቲ አጋ ኢትዮጵያዊ 02:20:40
2ኛ ሄለን ቶላ ኢትዮጵያዊ 02:21:01
3ኛ ሺሩ ደምሴ ኢትዮጵያዊ 02:21:05